Saturday, November 20, 2010

God's answer to our prayer.

www.tewahedo.se
የእግዚአብሔር መልስ፡-
ሌጄ ሆይ!

በብዙ ሀሳብ እና ጭንቀት፤እንቅልፍም በማጣት ቀናትን እንዳሳለፍክ አያለሁ።

ሰው ራሱን ከሚጎዳው በላይ  አንዳች የሚጎዳው ነገር የለምና ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው አንተ እንጅ እኔ አይደለሁም። ነገር ግን እኔ አባትህ ከምትችለው በላይ ትፈተን ዘንድ አልፈቅድምና ችግሮችህን ሁሉ በሠላም ታልፋቸዋለህ።

ምን ጊዜም ቢሆን በፍርሃትና በጭንቀት እንዳትወድቅ እኔ ለአንተ የገባሁልህ ቃል ኪዳንና የማደርግሌህን ጥበቃ አትርሳ። ችግር በገጠመህ ጊዜ ሁለ እኔ አባትህ እንደምጠብቅህና እንደምንከባከብህ አስታው። ለነፍስህ እረፍት እንድታገኝ በጭንቀትህ ሰዓት እኔ የተናገርኳቸው ቃላት ፊት ለፊት አስቀምጣቸው… “በህይወትህ ዕድሜ ሁለ ማንም አይቋቋምህም፤  አልጥልህም…አልተውህም” ኢያ.1፡5 “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ ማንም ክፉ ሉያደርግብህ የሚነሳ የለምና አትፍራ” ሐዋ.18፡10
ሌጄ ሆይ!

የሚፈራና የሚጨነቅ ሰው የእኔን ፍቅና ቃል  ኪዳን የረሳ ሰው  ስለ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይልቁን በአንተ ላይ  የሚደረገው ነገር ሁለ ከእኔ ፈቃድ ውጭ እንልሆነ ልትገነዘብ ያስፈልጋል። እንኳን  ሌላ የራስ ፀጉርህም በእኔ ዘንድ የተቆጠረ ነው።
ይህ ሁለ የተስፋ ቃሌ በፈተና ጊዜ ከሚመጣ ከጥርጥር ውጊያ ሊታደግህ ይችላል። ስለዚህ እኔ ለአንተ በምሰራልህ ሥራ ላይ መተማመን፤ተስፋንና ጥልቅ እምነትን የሚያረጋግጡ ጥቅሶችን በልብህ አጥናቸው፤በህሊናህ ውስጥ አስቀምጣቸው፤እንዳትረሳቸው መልሰህ ድገማቸው
ሁሌ ጊዜ በእኔ ደስ  ይበልህ፤ በአንተ ውስጥ ያለችውን ነፍስ በአርአያና በአምሳሌ የፈጠርኳት እኔ  ስለሆንኩ ከእኔ በስተቀር ይህችን ነፍስ ማንም ሊያስደስታት አይችልም። ከእኔ ተለይተህ በመኖር ደስታን አገኛለሁ  ብለህ ፈጽሞ አታስብ።
ምንም ነገር ቢሆን ሁለም ለበጎ ነውና እኔ ከአንተ ጋር እስከሆንኩ ድረስ በአንዳች አትከፋ። በጭንቀትህ ወቅትም አብሬህ እንደምጨነቅ ልብ በል።

የተስፋን ቃል የሰጠሁህ እኔ አባትህ ታማኝ ነኝና ባለህበት ቦታ ሆነህ በፍቅር ጠብቀኝ።ጆሮዬን ወደ አንተ ዘንበል አድርጌ ጩኸትህን እሰማለሁ፤ እንባህንም ከዓይንህ ላይ አብሳለሁ፤ አንተም በሁለት እግርህ ቆመህ ማዳኔን በሰው ሁሉ ፊት ትመሰክራለህ።

2 comments:

  1. wow...thank you so much brother! May Our Lord Jesus Christ bless our Congregation and include us in His Kingdom, Amen! I think this blog will be crucial in organizing our weekly activities and to let us know the things we should do before every Sunday!!!!

    May the intercession of Our Blessed Virgin Mary and all Saints be with all of us , Amen!!!!

    Kiros,

    ReplyDelete
  2. Thank you very much brother! Yes indeed it will help us a lot!
    God bless you!

    ReplyDelete