የእግዚአብሔር መልስ፡-(2)
ልጄ ሆይ!
•ጌታን ስትጠብቀው ቢዘገይብህ እንዲህ በል…
* * *
“በእግርጥ ጌታ ይመጣል …መቼ እንደሚመጣ ግን አላውቅም። ከእኔ የሚጠበቀው የሚመጣበትን ቀን ማወቅ ሳይሆን እንደሚመጣ ማመን ነው።”
* * *
•በመከራና በፈተና ውስጥ ስትሆን ደስታ እንዳይርቅህ እንዲህ በል…
* * *
“መከራና ፈተና በአማኝ ውስጥ ደስታን እንጂ ጭንቀትን አይፈጥሩም!!”
* * *
•ተስፋ እንዳትቆርጥ ይህን መዝሙር ከዳዊት ጋር ዘምር…
* * *
“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ” መዝ.26፡14
· ችግር ሲገጥምህ እንዲህ በል…
* * *
“እኔ ባላውቅም ከዚህ ችግር በስተጀርባ አንድ በጎ ነገር አለ…ማንኛውም አይነት መጥፎ ነገር ቢኖርም እንኳን አንተ ቸር እና ሰውን የምትወድ አምላክ ስለሆንክ ለበጎ አድርገህ ትቀይረዋለህ”
* * *
· ሰይጣን በኃጢአትህ ተስፋ እንዳያስቆርጥህ በልብህ እንዲህ በል…
“በሰዎች ዘንድ ያለው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ጋር ሲነጻጸር በውቅያኖስ ውስጥ እንደተጣለ ፍንጣቂ ጭቃ ይቆጠራል”
· ለጸሎት በቆምክ ጊዜ ማለት ስላለብህ ነገር ብዙ አትጨነቅ…
* * *
“እግዚአብሔር አምላክ ገና ፊቱ ስትቆም ቃላቶችህን ከመናገርህ በፊት ምን ማለት እንደፈለግህ የልብህን ያውቃልና፤ ሳትለምነው ምን እንደምትሻ ያውቃልና…”
(አምላክህ አልፋና ዖሜጋ እግዚአብሔር)